በአነስተኛ አማራጭ ግብር አከፋፈል ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ተሰጠ

1.24x1.24 (2)

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ነጋዴዎች በግሉ ዘርፍና በመንግስት የምክክር መድረክ ካነሷቸው በርካታ ሃሳቦች መካከል በጅምላ ንግድ የተሰማሩ ነጋዴዎች ላቀረቡት ጥያቄ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ እንደተለመደው የሚከተለውን ፈጣን ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ለዚህም ፈጣን ምላሽ በንግዱ ማህበረሰብ ስም ለቢሮው ኃላፊዎችና ማኔጅሜንት ልባዊ ምስጋናችንን እያቀረብን የተጻፈውን ሰርኩላር ደብዳቤ ማያያዛችንን እንገልጻለን፡፡በመሆኑም በክልላችን የሚገኙ ሁሉም መዋቅሮች በተቀላጠፈ ሁኔታ የተላለፈውን ሰርኩላር በመተግበር የንግዱን ማህበረሰብ ጥያቄ በመመለስ የተቀናጀ ስራ በመስራት የክልሉን ብልጽግና በጋራ እውን እንድናደርግ እንጠይቃለን፡፡

አማራጭ አነስተኛ ግብር በሚወሰንበት ዓመት ግብር ከፋዩ ሊከፍል የሚገባው በዓመቱ ባገኘው ጠቅላላ ገቢ ላይ ወይም ባገኘው የኮሚሽን ገቢ ላይ መሆኑ በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 አንቀጽ 23 የተገለፀውን በሚመለከት በአከፋፋዮች ወይም በጅምላ ሻጭ ነጋዴዎች እና በንግድ ወኪሎች መካከል ያለውን ልዩነት መገንዘብና የግብር ከፋዮቹን የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውን ውል እና ጠቅላላ የሥራ እንቅስቃሴ መመልከት ያስፈልጋል፡፡

    በዚህ መሠረት፡-

1.  ምርት ተረክበው የሚያከፋፍሉ ግብር ከፋዮችን በተመለከተ

ፋብሪካው ወይም አስመጪው የምርቱን የመሽጫ ዋጋ በሚተምንበትና አክፋፋዮቹ የትርፍ ህዳጋቸውን ከፍ/ዝቅ ማድረግ የማይችሉ በሚሆንበት ጊዜ ግብር ከፋዮች ላይ አማራጭ አነስተኛ ግብር የሚሰላው በኮሚሽኑ ዋጋ ወይም  ጠቅላላ ገቢ ላይ መሆኑን፣

2.  የንግድ ወኪሎች በተመለከተ 

የንግድ ወኪሎች የዋናውን ነጋዴ ዕቃ በውክልና ተረክበው የሚሸጡ የሸጡበትን ዋጋ ለወካያቸው ገቢ የሚያደርጉ እና ደረስኝ የሚቆረጠውም በወካዩ ነጋዴ ስም ሲሆን፣ ለወኪሎቹ የሚከፈላቸው የኮሚሽን ክፍያ ብቻ ነው:: ስለሆነም የንግድ ወኪሎችን በተመለከተ ለአማራጭ አነስተኛ ግብሩ የሚሰላው በሚያገኙት የኮሚሽን ክፍያ ላይ ብቻ መሆኑን፣

3.  ጅምላ ሻጮች / አከፋፋዮች በተመለከተ

ጅማላ ሻጮች / አከፋፋዮች በስማቸው የማከፋፈል የጅምላ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው ከአምራቹ ወይም ከአስመጪው የቃዎችን ግዢ ፈጽመው ለሌሎች ጅምላ ሻጮች ወይም ቸርቻሪዎች የሚሽጡ፤ በስማቸው ደረሰኝ የሚቆርጡ እና ክፍያ የሚቀበሉ ከሆነ የአማራጭ አነስተኛ ግብር ማስከፈያ መሰረቱ አመታዊ ጠቅላላ ገቢው ይሆናል፡፡ ነገር ግን ጅምላ ሻጩ/አከፋፋዩ ከአምራቹ ወይም ከአስመጪው ጋር ባደረገው ውል የገዛቸውን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ለሌሎች ጅምላ ሻጮች ወይም ቸርቻሪዎች የሚሸጥበት ዋጋ እና ጅምላ ሻጩ የሚያገኘው መቶኛ የተወሰነ ከሆነ  የአማራጭ አነስተኛ ግብሩ ተፈጻሚ የሚሆነው በአዋጁ አንቀጽ 23 መሰረት በጠቅላላ የሽያጭ ገቢው ላይ ሳይሆን ለጀምላ ሻጩ  ከላይ በተጠቀሰው ውል ወይም በህግ ስልጣን በተሰጠው አካል በተፈቀደለት መቶኛ ላይ ብቻ በመሆኑ፣

      ከላይ በዝርዝር በተገለጹት ማብራሪያዎች መሠረት አማራጭ አነስተኛ ግብር በሚወሰንበት ጊዜ  ተፈጻሚ እንዲሆን እናሳስባለን በማለት ይህንን ሰርኩላር ደብዳቤ ለሚመለከታቸው አስተላልፏል፡፡

1.24x1.24 2 1022x1024
logo
ደቡብ ኢትዮጵያ ገቢዎች ሰርኩላር Pdf 724x1024

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top