የገቢዎች ሚኒስቴር በልብስ ስፌት አገልግሎት ላይ የሚጣለውን የኤክሳይዝ ታክስ አከፋፈል በተመለከተ አዲስ ማብራሪያ ሰጥቷል።

photo 2026 02 11 00 19 52

ሚኒስቴሩ፣ የልብስ ስፌት ፋብሪካዎች " የአገልግሎት ሰጪ ነን " በሚል ምክንያት ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ መሆን እንደማይችሉ ባወጣው ሰርኩላር ደብዳቤ ላይ አመልክቷል።

ከዚህ ቀደም የገንዘብ ሚኒስቴር በሰጠው ማብራሪያ፣ አምራቾች ከደንበኞች የሚቀርብላቸውን ጨርቅ የመስፋት አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት የኤክሳይዝ ታክስ እንዲከፍሉ አይጠየቁም ተብሎ የነበረ ቢሆንም፣ ይህ አሰራር የታክስ ገቢ እንዲታጣ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።

በመሆኑም በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 (እንደተሻሻለው) መሠረት፣ በHS Code 50.07 እስከ 63.04 የተመደቡ የጨርቃ ጨርቅና የተሰፉ ልብሶች ምርቶች የኤክሳይዝ ታክስ የሚጣልባቸው በመሆኑ፣ የልብስ ስፌት ፋብሪካዎች ግዴታቸውን እንዲወጡ መታዘዙን ካፒታል ጋዜጣ ዘገቧል።

የገንዘብ ሚኒስቴር በቁጥር ታ/ክ/4/5/952 በቀን 01/04/2018 በሰጠው አዲስ ማብራሪያ መሠረት፦ የኢንቨስትመንትና የንግድ ፈቃድ ያላቸው የልብስ ስፌት ፋብሪካዎች ለኤክሳይዝ ታክስ ዓላማ የመመዝገብ ግዴታ አለባቸው።

በተጨማሪም " የልብስ ስፌት አገልግሎት ሰጪ ነን" በሚል ሰበብ ከታክስ ነፃ መሆን አይችሉም የተባለ ሲሆን አምራች ፋብሪካዎችና የሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ይህንን አውቀው ተገቢውን ክትትል እንዲያደርጉ የገንዘብ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

በታህሳስ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በገቢዎች ሚኒስትር የተላለፈዉ ይህ ውሳኔ በዘርፉ ሊሰበሰብ የሚገባውን የታክስ ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብና አሰራሩን ግልፅ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የካፒታል ጋዜጣ ነው።

photo 2026 02 11 00 19 52

photo 2026 02 11 00 19 55

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top